ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
BBC News, አማርኛ - ዜና
ዜና
በፌደራሉ ሠራዊት እና በትግራይ ኃይሎች መካከል ግጭት መቀስቀሱ ተገለጸ
ከሱዳን ጋር በሚዋሰነው የሰሜናዊ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክፍል ውስጥ በሚገኝ አካባቢ በፌደራል መንግሥቱ ሠራዊት እና በትግራይ ኃይሎች መካከል ዛሬ ማለዳ ላይ ግጭት መቀስቀሱን የተለያዩ ምንጮች አመለከቱ። አዲስ የተቀሰቀሰውን ግጭት በመጀመር በህወሓት የሚመራው የትግራይ ክልል አስተደዳር እና የፌደራል መንግሥቱ ከፍተኛ ባለሥልጣን አንዳቸው ሌላኛቸውን ከስሰዋል።
ሙዚቃ በሱቅ፣ በወጥ ቤት፣ በወፍጮ ቤት፣ በጋራዥ. . . የሚያጫውቱት ዲጄዎች
ዲጄ ሲባል መጀመሪያ የሚመ��ልን ምሥል ምናልባትም የዳንስ ወለል ላይ ወዝ ወዝ የሚሉ ሰዎች እና ብልጭ ድርግም የሚል መብራት ይሆናል። እነዚህ ዲጄዎች ግን ማንኛውንም ቦታ ለሙዚቃቸው መዳረሻ ማድረግ የሚችሉ ናቸው። ጋራዥ፣ ቴአትር ቤት፣ ፀጉር ቤት፣ መጻሕፍት መደብር፣ ልብስ ሰፊ ቤት፣ ግንባታው ያልተጠናቀቀ 40/60፣ ሸክላ ሠሪ ቤት፣ ወፍጮ ቤት፣ ውይይት ታክሲ. . . የማይገቡበት የለም።
ቀጥታ, አሜሪካ በኢራን የኤነርጂ ተቋማት ላይ ያነጣጠረ መጠነ ሰፊ ጥቃት ለመፈጸም አቅዳለች ተባለ
የአሜሪካ ጦር በዚህ ሳምንት መጨረሻ በኢራን ላይ አዲስ ጥቃት ለመክፈት እየተዘጋጀ መሆኑን ስማቸውን ያልጠቀሷቸውን ምንጮች ተጠቅመው የአሜሪካ መገናኛ ብዙኃን ዘገቡ። ለሲቢኤስ መረጃ የሰጡ ምንጮች ጥቃቱ የኢራንን የኃይል መሠረተ ልማቶች ላይ ሊያተኩር እንደ��ችል ጠቅሰው ነገር ግን ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ይሁንታ መስጠት አለባቸው ብለዋል።
አሜሪካ ከኢትዮጵያ እና ከሌሎች የአፍሪካ አገራት የምትፈልጋቸው የጤና መረጃዎች ምንድን ናቸው? ከሉዓላዊነት ጋርስ ምን ያገናኘዋል?
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ወደ ሥልጣን ከተመለሱ እና ግዙፉን የአሜሪካ የእርዳታ ድርጅት ካፈረሱ በኋላ ለአፍሪካ አገራት የምትሰጠውን ድጋፍ አካሄድ ቀይራለች። ለዚህ ደግሞ ተቃውሞ እና ጥያቄ ያስነሳው ኢትዮጵያን ጨምሮ ከበርካታ የአፍሪካ አገራት ጋር የተፈራረመችው የጤና መረጃ ስምምነት ተጠቃሽ ነው።
ቢቢሲ አማርኛ በቲክቶክ
አስተማማኝ ዜና እና መረጃን ቅድሚያ ለማግኘት ቢቢሲ አማርኛን ቲክቶክ ላይ ይከተሉ
የቢቢሲ አማርኛ ዩቲዩብ ቪድዮዎች
ቪዲዮ, ኢትዮጵያዊው የማይክሮሶፍት ባለሙያ ስለኤአይ ጥቅም እና ጉዳት ምን ይላሉ?
ዓለማችንን በማይታመን ፍጥነት እየለወጠ ያለውን ��ው ሠራሽ አስተውሎት (ኤአይ) በአግባቡ መገንዘብ ምርጫ ሳይሆን ግዴታ እየሆነ የመጣ ይመስላል። ስለ ሰው ሠራሽ አስተውሎት የተዛቡ ምልከታዎች ምንድን ናቸው? ለወደፊቱ የኤአይ ዓለም እንዴት እራሳችንን ማዘጋጀት እንችላለን? የሚሉና ተያያዥ ጥያቄዎችን በተመለከተ ኢትዮጵያዊው የማይክሮሶፍት ባለሙያ ዶ/ር ግርማው አበበ ታደሰ ምላሽ ሰጥቷል።
ቪዲዮ, ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ስለምርጫ፤ ስለ���ሪቶሪያ፤ ስለአርሲ. . . ምን አሉ?
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተሰናባቹ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ላቀረቡላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽ የተለያዩ ወቅታዊ ጉዳዮችን አንስተዋል። ቢቢሲ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር ውስጥ አምስት ዋና ዋና ጉዳዮችን መርጦ አውጥቷል።
የቢቢሲ አማርኛ ዩቲዩብ ቻናልን ይቀላቀሉ
አነጋጋሪ ጉዳይ
ሌተናንት ጄነራል ታደሰ ወረደ 'በቁም እስ��� ላይ' ናቸው?
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደርን ለአንድ ዓመት ሲመሩ የነበሩት ሌተናንት ጄነራል ታደሰ ወረደ ከሥልጣናቸው ከተወገዱ ወዲህ ስለሚገኙበት ሁኔታ በግልጽ ሳይታወቅ ወራት ተቆጥረዋል። በዚህ ሳምንት በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ ወደ መቀለ ያደረጉትን ጉዞ ተከትሎ ስማቸው የተነሳው ሌተናንት ጄነራል ታደሰ፤ ስላሉበት ሁኔታ ከቅርብ ምንጮች ተጨባጭ መረጃ ማግኘት ተችሏል።
ፌደራል ፖሊስ "60" ስደተኞችን ለሞት ዳርገዋል የተባሉ 17 ሕገወጥ የሰዎች ዝውውር ተጠርጣሪዎች መያዛቸውን አስታወቀ
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ "ከ60 በላይ" ለሚሆኑ ስደተኞች ሞት እና "ለበርካታ ሴቶች" መደፈር ተጠያቂ ናቸው የተባሉ 17 "አደገኛ የሰዎች አዘዋዋሪዎች" በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን አስታወቀ። የመን ውስጥ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ላይ "ከፍተኛ ኢሰብአዊ ድርጊቶች" ይፈጽሙ ነበር የተባሉት እነዚህ ���ጠርጣሪዎች፤ "ከተጎጂዎች ከ1 ቢሊየን ብር በላይ" መሰብሰባቸውንም ገልጿል።
የአሜሪካው ልዑክ ከኤርትራ፣ ከግብፅ እና ከሶማሊያ ሚኒስትሮች ጋር ስለ ቀጣናው ደኅንነት መወያየታቸው ተገለጸ
የአረብ እና የአፍሪካ አገራት ጉዳዮች የአሜሪካ ከፍተኛ አማካሪ ማሳድ ቦውሉስ ከኤርትራ፣ ከግብፅ እና ከሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር የአፍሪካ ቀንድን ደኅንነት "በማጠናከር" ዙሪያ መወያየታቸው ተገለጸ። ከሚኒስትሮቹ ጋር የተናጠል ውይይት ያደረጉት የአሜሪካው ከፍተኛ አማካሪ፤ ስለ አፍሪካ ቀንድ "ሰላም፣ ደኅንነት እና መረጋጋት" ማንሳታቸውን በኤክስ ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ አስታውቀዋል።
አራት ሺህዎቹ የሀገራዊ ምክክር ተሳታፊዎች በአጀንዳዎች ላይ የሚወያዩት እንዴት ነው?
የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከአራት ዓመት በላይ ከወሰደ የተወካዮች መረጣ፣ አጀንዳ ማሰባሰብ እና ሌሎች ተግባራት በኋላ ዛሬ ረቡዕ ሐምሌ 8/2018 ዓ.ም. የመጨረሻውን የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ያስጀምራል። በአዲስ አበባ ከተማ 'አዲስ ኮንቬንሽን ሴንተር' በሚካሄደው በዚህ ጉባኤ ላይ ከተለያዩ ክልሎች፣ ወረዳዎች፣ ከፌደራል እንዲሁም በውጭ አገራት ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የተወጣጡ ከአራት ሺህ ሰዎች ይሳተፋሉ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት ላይ ማሻሻያ ሊኖር እንደሚችል ፍንጭ ሰጡ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ በተጀመረው ሀገራዊ ምክክር የመጨረሻ ጉባኤ መክፈቻ ላይ በአገሪቱ ሕገ መንግሥት ላይ ማሻሻያ ሊኖር እንደሚችል ፍንጭ ሰጡ። ከአራት ዓመታት በላይ በዋና ዋና አገራዊ ጉዳዮች ላይ አጀንዳ ሲያሰባስብ እና ተወያዮችን ሲያስመርጥ የቆየው ሀገራዊ ምክር ኮሚሽን የመጨረሻውን ምክክር የሚያደርግበትን ጉባኤ ዛሬ ረብዑ ሐምሌ 8 2018 ዓ.ም. ���ዲስ አበባ ላይ ተጀምሯል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ "ሰዎች በነጻነት ተንቀሳቅሰው መሥራት የማይችሉበት ደረጃ" ላይ መደረሱን ኮነኑ
በአማራ ክልል ደብረ ማርቆስ ከተማ የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፤ "ሰዎች በነጻነት ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሰው ሥራ መሥራት ወደማይችሉበት ደረጃ" መደረሱን "አጠያያቂ፣ ጥዩፍ እና የማይገባ" ሲሉ ኮነኑ። በታጣቂዎች ምክንያት የተፈጠሩ የእንቅስቃሴ መገደቦችን የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ወደ ደብረ ማርቆስ ከተማ የሚደረግ የመኪና ጉዞ "በኛ ጥረት መመለስ ይኖርበታል" ሲሉም ተናግረዋል።
የተወሰኑ የአፍሪካ አገራት ለምን ኢትዮጵያ የፈረመችውን የትራምፕ የእርዳታ ስምምነት ውድቅ አደረጉ?
አሜሪካ ዓለም አቀፍ የእርዳታ ተቋሟን ከዘጋች በኋላ በውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቷ በኩል አዲስ ዓለም አቀፍ የጤና ስትራቴጂ ዘርግታለች። በዚህ አሰራር ድጋፍ የሚያገኙ መንግሥታት እንደ የጤና መረጃዎችን ለአሜሪካ ማጋራት ያሉ ኃላፊነቶች ተጥሎባቸዋል። አገራት እና ተቋማት አሰራሩ ላይ ተቃውሟቸውን እያሰሙ ነው። ለምን?
ቢቢሲ አማርኛን በዋትስአፕ ላይ ያግኙ
የመካከለኛው ምሥራቅ ጦርነት
የተባበሩት አረብ ኤምሬቶችን ቀጣናዊ ፖሊሲ የለወጠው የኢራን ጦርነት
የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ከአሜሪካ እና ከእስራኤል ጋር ባላት ግንኙነት የተነሳ የኢራን ዋነኛ ዒላማ ከሆነች በኋላ በቀጣናው አገራት ላይ ያላት መተማመን እየቀነሰች ነው። ለፖለቲካ፣ ለምጣኔ ሃብት እና ሌሎች ፍላጎቷን ለማሟላት ከቀጣናው ውጭ መመልከትን መርጣለች። ለዚህም ከሕንድ፣ ከዩክሬን፣ ከግሪክ፣ ከቆጵሮስ እና ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ትስስር እያጠናከረች ነው።
የአሜሪካ እና ኢራን ጦርነትን ያስቆማል የተባለው ስምምነት ምን ምን ይዟል?
የአሜሪካ እና ኢራን ከመግባባት ላይ የደረሱበት ሰነድ ይፋ ሆኗል። ስምምነቱ የሆርሙዝ ወሽመጥ እንዲከፈት እንደሚያደርግ እንዲሁም ለወራት የቆየውን ጦርነት ያስቆማል የሚል እምነት አሳድረዋል። ትራምፕ ባለ 14 ነጥቡ ስምምነት "በአፈጻጸም ላይ የተመሠረተ" መሆኑን እና ኢራን ልትጠቀም የምትችለው ስምምነቱን የምታከብር ከሆነ ብቻ ነው ብለዋል። የስምምነቱ ነጥቦች ምን ምን ይዘዋል?
በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ የአሜሪካንን ባሕር ኃይል እየፈተኑ ያሉት የኢራን ትናንሽ ጀልባዎች
ፕሬዝዳንት ትራምፕ የኢራንን ባሕር ኃይል እንዳወደሙ ቢናገሩም፣ ኢራን ትናንሽ ፈጣን ጀልባዎችን በመጠቀም በሆርሙዝ ወሽመጥ የመርከቦችን እንቅስቃሴን መግታት ችላለች። ስለእነዚህ ውጤታማ የኢራን ፈጣን ወታደራዊ ጀልባዎች ምን እናውያለን?
አሜሪካ እና ኢራን ድል እንደተቀዳጁ እያወጁ ባሉበት ጦርነት አሸናፊው ማን ነው?
አሜሪካ ከኢራን ጋር የምታደርገውን ጦርነት ማቆሟን እየተናገረች ነው። በሁለቱ አገራት መካከል የተኩስ አቁም ከተደረገ ከሳምንታት በኋላ ማክሰኞ ዕለት የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ "ኢፒክ ፊውሪ' በማለት የተጠራው ዘመቻ ማብቃቱን ተናግረዋል።በአሜሪካ እና በኢራን መካከል በተደረገው ጦርነት ማን አሸነፈ?
የኢንተርኔት ዳታን በመቆጠብ የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽን በቀላሉ ማንበብ ይፈልጋሉ?
የቢቢሲ አማርኛን ድረ ገጽ በቀላሉ በመክፈት ዜና እና ታሪኮችን በጽሑፍ ብቻ ያንብቡ!
ከየፈርጁ
በድምጻውያን ጉሮሮ ላይ የቆመው ኤአይ የኢትዮጵያን ሙዚቃ መልክ እንዴት ሊለውጠው ይችላል?
በሰው ሰራሽ አስተውሎት (ኤአይ) ተገርበው በአዲስ መልክ የተሠሩ ሙዚቃዎች የዩቲዩብ ገፆችን ወርረዋል። የአንጋፋ እና ተወዳጅ ድምጻውያን የሙዚቃ ሥራዎች አማርኛው በተኮላተፈ የኤአይ አንደበት እየተዘፈኑ ነው። አንዳንዶቹ በመቶ ���ህዎች የሚቆጠሩ ዕይታዎች አሏቸው። የአድማጭን ትኩረት የሳቡም ይመስላሉ። ለመሆኑ የዘመኑ የቴክኖሎጂ ልህቀት በተለይ በሙዚቃው ዘርፍ ምን ያሳጣ፣ ምን ያስገኝ ይሆን? የኢትዮጵያን ሙዚቃስ በምን መልኩ ሊለውጠው ይችላል?
አጃኢብ!
የተመለሱ ጥያቄዎች
ያለባቸው የጤና ችግር ሕክምና እንዲያጠኑ ያደረጋቸው ኢትዮጵያውያን ወጣቶች
በረከት በቀለ፣ ኪምቢፊዳ በሚል ስም ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ይታወቃል። ወደ ቲክቶክ ብቅ ከማለቱ አስቀድሞ "በስፓይና ቢፊዳ (spina befida) የተያዝኩ ብቸኛው ሰው እኔ ብቻ እንደሆንኩ ይሰማኝ ነበር" ይላል። የአሊያንስ ፎር በርዝ ዲፌክት መሥራቹ ዶ/ር ነቢያት ተስፋዬም ልክ እንደ በረከት ሁሉ ከስፓይና ቢፊዳ (የነርቭ ዘንግ ክፍተት) ጋር ነው የተወለደው። አሁን 33 ዓመት እንደሆነው የሚናገረው ዶ/ር ነቢያት፣ በተወለደ በ22ኛው ቀን የስፓይና ቢፊዳ የቀዶ ሕክምና ተደርጎለታል። ሁለቱም ወጣቶች ከራሳቸው ህመም ተነስተው ሕክምና ለማጥናት መወሰናቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል።
ሌላ ዕይታ
ቢቢሲ አማርኛን በማኅበራዊ ሚዲያዎች ይከታተሉ
የዓለም ዋንጫ - 2026
አዳዲስ ታሪክ የሚመዘገብበት 23ኛው የዓለም ዋንጫ ውድድር ሙሉ መረጃን እዚህ ያገኛሉ
የዓለማችን ትልቁ የእግር ኳስ ውድድር የዓለም ዋንጫ በ23ኛ ዙር ውድድር በርካታ አዳዲስ ነገሮች የሚታዩበት ሆኖ ከሰኔ 4 አስከ ሐምሌ 12 ድረስ ይካሄዳል። በውድድሩ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ሦስት አገራት ውስጥ የሚካሄደውን የዓለም ዋንጫ ተጎራባቾቹ አሜሪካ፣ ሜክሲኮ እና ካናዳ ያስተናግዱታል። የውድድር ቦታዎች፣ ቀናት፣ ሰዓታት፣ ውጤቶች፣ የምድብ ድልድል እና ደረጃ እንዲሁም ሌሎች የጨዋታ ዝርዝር መረሃ ግበሮች እዚህ ይቀርባሉ።